Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ ፖለቲካ ሃይሎች ግጭትን ከሚያባብሱ ድርጊቶች እንዲቆጠቡ ጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የሶማሊያ ፖለቲካ ሃይሎች በሀገሪቱ የተፈጠረውን ግጭት የሚያባብሱ ድርጊቶችን ከመፈጸም እንዲቆጠቡ ጥሪ አቅርቧል፡፡

በሞቃዲሹ በመንግሥት ወታደሮችና በተቃዋሚ ታጣቂዎች መካከል በምርጫ መዘግየት ምክንያት የተፈጠረው ውጥረት ተባብሶ መቀጠሉ ተገልጿል፡፡

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ÷ በሶማሊያ የፖለቲካ ሃይሎች መካከል በተፈጠረው ግጭት ሳቢያ በሀገሪቱ የተከሰተው አለመረጋጋት እንዳሳሰበው አስታውቋል፡፡

ኮሚሽኑ ሁሉም ተፋላሚ ሃይሎች ግጭቱን በፍጥነት እንዲያቆሙ እና ውጥረቱን ይበልጥ ከሚያባብሱ ድርጊቶች እንዲቆጠቡ አሳስቧል፡፡

የሶማሊያ ፖለቲካ ሃይሎች ልዩነታቸውን በሰለጠነ መንገድ በጠረጴዛ ዙሪያ በአካታች ውይይት እንዲፈቱም ጥሪ አቅርቧል፡፡

በሞቃዲሾ የተፈጠረውን የጸጥታ ችግር በቅርበት እንደሚከታተል የጠቆመው ህብረቱ ÷ ሀገሪቱን ወደ ቀደመ ሰላሟ ለመመለስ በሚደረገው ጥረት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.