ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕና ዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን የ80 ሚሊየን ዶላር የብድር ስምምነት ተፈራረሙ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ እና ዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን የ80 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር የረጅም ጊዜ የብድር ስምምነት ተፈራርመዋል።
ስምምነቱን የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጀማል አህመድና የዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን የአፍሪካ ቀጣና ምክትል ፕሬዚዳንት ኢትዮጲስ ተፈራ በኬንያ ናይሮቢ ነው የተፈራረሙት።
አቶ ጀማል አሕመድ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ከዓለም አቀፉ የፋይናንስ ተቋም ጋር የተጀመረው አጋርነት የሀገሪቱን የሆስፒታሊቲ ዘርፍ ለማዘመን እንዲሁም በኢትዮጵያ ቀጣይነት ያለው የሥራ ዕድል ፈጠራን ለማጠናከር ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።
ኢትዮጲስ ተፈራ በበኩላቸው÷ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የአገልግሎት ዘርፉን የበለጠ እንዲያዘምንና ተጨማሪ የሥራ እድል እንደፈጥር ስምምነት ላይ ተደርሷል ብለዋል።
በተገኘው ገንዘብ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ሸራተን አዲስ ሌግዠሪ ኮሌክሽን ሆቴልን በዘመናዊ መልኩ እንደሚያድስ ተገልጿል።
በሸራተን ደረጃ አዲስ ሆቴል እንደሚገነባም የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ለፋና ዲጂታል በላከው መረጃ አመላክቷል።