Fana: At a Speed of Life!

ሪያል ማድሪድ ኩኩሬላን ማስፈረሙን ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የስፔኑ ክለብ ሪያል ማድሪድ ማርክ ኩኩሬላን ከቼልሲ ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል፡፡

ስፔናዊው የግራ መስመር ተጫዋች በሪያል ማድሪድ ቤት እስከ ፈረንጆቹ 2032 ድረስ የሚያቆየውን ውል ነው የተፈራረመው፡፡

ሪያል ማድሪድ ለ27 ዓመቱ ተጫዋች 55 ሚሊየን ዩሮ እና እየታየ የሚጨመር 5 ሚሊየን ዩሮ የዝውውር ሒሳብ የሚከፍል ይሆናል፡፡

ኩኩሬላ የምዕራብ ለንደኑን ክለብ ቼልሲ በ2022 ከብራይተን መቀላቀሉ ይታወሳል፡፡

ተጫዋቹ በቼልሲ በነበረው ቆይታ የኮንፈረንሰ ሊግ እና የዓለም ክለቦች ዋንጫዎችን ማሸነፉ አይዘነጋም፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.