Fana: At a Speed of Life!

በሳይበር ደኅንነት ላይ ትኩረቱን ያደረገ አሕጉር አቀፍ ጉባኤ…

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሳይበር ደኅንነት ላይ ትኩረቱን ያደረገ አሕጉር አቀፍ ጉባኤ የፊታችን ሰኔ 17 እና 18 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡
ጉባኤው የሳይበር ደኅንነት ማህበር ከኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር እንዲሁም ከተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ጋር በመተባበር የሚዘጋጅ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የአፍሪካ ሀገራት የዲጂታላይዜሽን ጉዞ ደኅንነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ጥናታዊ ጽሑፎች በጉባኤው እንደሚቀርቡም ተመላክቷል።
እንዲሁም ሀገራት ያላቸውን ተሞክሮ የሚያካፈሉበት፣ የቴክኖሎጂ ተቋማት በዘርፉ ያቀረቧቸውን አማራጮች የሚያስተዋውቁበት ስለመሆኑም ጉባኤውን አስመልክቶ በተሰጠው መግለጫ ተነስቷል፡፡
ጉባኤው የመንግሥት ተቋማት በዲጂታል ሥርዓት ያላቸውን ተሳትፎ ደኅንነቱ የተጠበቀ ለማድረግና የአሕጉሪቱን የላቀ ትብብር ለማረጋገጥ እንደሚያግዝ ታምኖበታል።
መርሐ ግብሩ ፖሊሲ አውጪዎችን፣ የቴክኖሎጂ አልሚዎችን እና የዘርፉ ተመራማሪዎችን የሚያገናኝ እንዲሁም ተጨባጭ ምክረ ሐሳቦች የሚያገኙበት እንደሚሆንም ይጠበቃል።
መድረኩ አፍሪካዊ ጉዳዮችን በአፍሪካዊ የመፍትሄ ቅኝት የመፍታትና ፓን አፍሪካኒዝምን በዲጂታሉ ዘርፍ የማረጋገጥ አንዱ ማሳያ መሆኑም ተገልጿል።
በሔኖክ ለሜ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.