Fana: At a Speed of Life!

ለ30 ዓመታት የተቋረጠውን ጉዞ እንደ አዲስ ያስጀመረው የደብረ ማርቆስ ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት አውሮፕላን ማረፊያ…

መሠረተ ልማቱ በአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ማርቆስ ከተማ የተገነባ ሲሆን፣ አካባቢውን ዳግም ከሌሎች አካባቢዎች ያገናኘ ዘመናዊ የአውሮፕላን ማረፊያ ነው።
የአካባቢው የአውሮፕላን ማረፊያው አገልግሎት ለ30 ዓመታት ያህል ተቋርጦ ከቆየ በኋላ፣ በዘመናዊ መልክ ተሻሽሎና ደረጃው ከፍ ብሎ ተገንብቶ ዛሬ ሐምሌ 5 ቀን 2018 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በይፋ ተመርቋል።
የአውሮፕላን ማረፊያው 2,400 ሜትር ርዝመት እና 30 ሜትር ስፋት ያለው የማኮብኮቢያ መንገድ አለው።
ይህም እንደ Q400 (የሕዝብ) እና Boeing 737 ያሉ ግዙፍ የሕዝብና የጭነት አውሮፕላኖችን ማሳረፍ የሚያስችል ከፍተኛ አቅም ያለው መሆኑን ልብ ይሏል።
ባለፉት ጥቂት ዓመታት ግንባታቸው ተጠናቅቆ አገልግሎት መስጠት ከጀመሩት የሀገር ውስጥ አውሮፕላን ማረፊያዎች 5ኛው ሲሆን፣ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ውስጥ 25ኛው የሀገር ውስጥ አውሮፕላን ማረፊያ ነው።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ ደብረ ማርቆስ በሳምንት ሦስት ቀናት የሚመላለስ መደበኛ የበረራ አገልግሎት ይሰጣል።
ለዚሁ በረራ በዋናነት ጥቅም ላይ የሚውለው DHC-8-Q400 turboprop የተባለው የመንገደኞች አውሮፕላን ነው።
የአውሮፕላን ማረፊያው የምሥራቅ ጎጃም ዞን እና የአካባቢውን የንግድ፣ የኢንቨስትመንት እና የሎጂስቲክስ እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ ያነቃቃል።
ወደ ሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ ታሪካዊና ተፈጥሯዊ የቱሪስት መስህቦች የሚጓዙ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ጎብኚዎችም ጉዟቸውን በቅልጥፍና እንዲያከናውኑ ትልቅ በር ይከፍታል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.