Fana: At a Speed of Life!

ልማትና ሰብዓዊነት በበጎ ፈቃድ አገልግሎት …

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የነገዋን የበለጸገች ኢትዮጵያን በመቅረጽ ረገድ ከፍተኛ ድርሻ አለው፡፡

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ አደጋ በሚፈጠር ችግር እርስ በርስ በመደጋገፍ እና በመተሳሰብ ክፉ ቀናትን በጋራ የማለፍ ባህል ነዉ።

በኢትዮጵያ የክረምትና የበጋ ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሐ ግብሮች ተቀርጸው በጎ ፈቃደኛ ባለሃብቶች፣ ወጣቶችና መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጉልበታቸውን፣ ገንዘባቸውን፣ ጊዜያቸውንና እውቀታቸውን ያበረክታሉ፡፡

የቤት ግንባታ፣ ማዕድ ማጋራት፣ የደም ልገሳ፣ የትምህርት ቁሳቁሶች ድጋፍ እና የአካባቢ ጥበቃን ጨምሮ የተዘረጉ የበጎ ፈቃድ ተግባራት የበርካታ ዜጎችን ሕይወት ቀይረዋል፡፡

ይህ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የዘወትር የልማት እና የሰብዓዊነት አጀንዳ ሆኖ ቀጥሏል፡፡

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ኃላፊነት የሚሰማው ዜጋ በመፍጠር ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል፡፡

ወጣቶች ከሚኖሩበት አካባቢ በተጨማሪ ወደ ሌሎች አካባቢ በመሄድ ጭምር የተለያየ ቋንቋ እና ባህል ካላቸው ማህበረሰቦች ጋር በጋራ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ይሰጣሉ፡፡

በዚህም በህብረተሰቡ መካከል ጠንካራ የመተሳሰብ ድልድይ ለመገንባት እንደሚያግዝ ይታመናል፡፡

ወጣቱ ትውልድ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ የሚያሳየው ከፍተኛ ተነሳሽነት ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና አካባቢያዊ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል አቅም እንዳለው ማሳያ ነው።

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከማህበራዊ ጠቀሜታው ባለፈ የተረጋጋ ማህበረሰብን ለመገንባት ያግዛል፡፡

በትዕግስት ግዛቸው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.