Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በአሚር ሼክ ሃማድ ቢን ካሊፋ አል ታኒ ህልፈት የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኳታር ሉሳይል ቤተ መንግሥት በመገኘት አሚሩ ሀማድ አል ታኒን እና ቤተሰባቸውን አጽናንተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በቀድሞ አሚር ሼክ ሃማድ ቢን ካሊፋ አልታኒ ሕልፈት የተሰማቸውን ሐዘን ለመግለጽ ትናንት ምሽት ኳታር መግባታቸው ይታወሳል፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉዞ በኢትዮጵያ እና ኳታር መካከል ያለውን የረጅም ጊዜ ጠንካራ ወዳጅነት የሚያሳይ ነው።
ከዚህ ባለፈም በቀጣናው እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ጉልህ አሻራ ጥለው ያለፉትን መሪ የሚያከብር መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
ጽሕፈት ቤቱ ለኳታር ሕዝብና መንግሥት መጽናናትን ተመኝቷል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.