Fana: At a Speed of Life!

እኛ ልዩነቶቻችንን የመፍታት ጠንካራ ባህል ያለን ህዝቦች ነን

ኢትዮጵያውያን በብዝኀነት ተከባብረን የምንኖር፣ ልዩነቶችን በውይይትና በሽምግልና የመፍታት ጠንካራ ባህል ያለን ህዝቦች ነን።

ይህ በጎ አኩሪ ልማዳችን ሀገራዊ ምክክሮችን እንድንጠቀምበት እና ዘላቂ ሰላምን በጋራ እንድንገነባ ትልቅ መሰረት ይሆነናል።

የኢትዮጵያ የምክክር ኮሚሽን ለዘላቂ ሀገራዊ መግባባት የቤት ሥራውን እየሠራ እንዳለው ሁሉ፤ በየአካባቢያችን ያሉ አለመግባባቶች እንዳይሰፉ በሽምግልና የሚፈቱት የሀገር ሽማግሌዎች የሰላም ምሰሶዎች ናቸው።

ችግሮችን በመነጋገር እና የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ የመፍታት በየአካባቢው በርካታ ሀገር በቀል ፀጋዎች አሉን፡፡

በጋራ ተሳስቦ የመኖር፣ አንዱ የሌላውን ባህል፣ እምነት እና ቋንቋ አክብሮ በብዝሃነት ውብ የሆነ አንድነትን የመፍጠር ልምዱም አለን፡፡

ላለፉት ዓመታት የቆዩትን ሀገራዊ ልዩነቶች ለመፍታት ደግሞ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ታላቁንና ታሪካዊውን ጉባኤ በማካሄድ ላይ ይገኛል።

ይህ ሂደት የህብረተሰብ ክፍሎችን በአንድ ላይ የሚያገናኝ አዲስ የሰላም መንገድ ነው።

በዚህም የየአካባቢውን የሽምግልናና የይቅርታ እሴት በመጠቀም በሀገራችን ዘላቂ ሰላም ማምጣት እንችላለን።

ይህንን የጋራ ዓላማ ለማሳካት ሁላችንም በየሚናችን በንቃት መሳተፍ አለብን።

መደማመጥና መግባባት የሀገር አንድነት ማስተማመኛ ናቸውና።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.