የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከ25 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ በጀት አጸደቀ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2018(ኤፍ ኤም ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ከ25 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ በጀት በማጽደቅ መደበኛ ጉባኤውን አጠናቅቋል።
የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ዚያድ አብዱላሂ የበጀት ዓዋጁን ባቀረቡበት ወቅት እንደገለጹት÷ በ2019 ዓ/ም ለክልሉ የተያዘው በጀት ካለፈው 2018 በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ30 በመቶ ዕድገት አሳይቷል፡፡
በጀቱ ከክልሉ ገቢ፣ ከፌዴራል ድጎማ፣ ዘላቂ የልማት ግቦች፣ ከዕርዳታ፣ ከተቋማት የውስጥ ገቢ እና ከሌሎችም ዘርፎች የሚገኝ መሆኑንም ጠቁመዋል።
ለ2019 በጀት ዓመት ከተያዘው አጠቃላይ በጀት ውስጥ ከ15 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በክልሉ ከሚሰበሰብ ገቢ ይሸፈናል ነው ያሉት።
የክልሉን ወጪ በራሱ የገቢ ምንጭ ለመሸፈን አበረታች ጥረት እየተደረገ ሰለመሆኑም ጠቁመዋል፡፡
በክልሉ በ2019 በጀት ዓመት ለመሰብሰብ የታቀደው ገቢ ካለፈው በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ40 በመቶ ጭማሪ እንዳለው የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል።
ለ2019 በጀት ዓመት የጸደቀው በጀት ለመደበኛ እና ለልማት ሥራዎች አገልግሎት ላይ እንደሚውልም ተመላክቷል።