ማንቼስተር ዩናይትድ ዌልሳዊውን ግብ ጠባቂ ኪት ማርጌሰን አስፈረመ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ማንቼስተር ዩናይትድ ኪት ማርጌሰንን ከስዋንሲ ሲቲ ለማስፈረም በቡድኖቹ መካከል ከስምምነት ላይ ተደርሶ ዝውውሩ ተጠናቅቋል፡፡
የ20 ዓመቱ ግብ ጠባቂ ኪት ማርጌሰን የመጀመሪያ ኢንተርናሽናል ጨዋታውን ባሳለፍነው መጋቢት ወር ለሀገሩ ዌልስ ከ 21 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ተሰልፎ ተጫውቷል።
የስዋንሲ ሲቲ አካዳሚ ፍሬ ለሆነው ግብ ጠባቂ ዝውውርም ማንቼስተር ዩናይትዶች የካሳ ክፍያ ለሻምፒዮንሺፑ ክለብ እንደሚከፍሉ ዘ አትሌቲክ ዘግቧል፡፡
ማንቼስተር ዩናይትዶች ቡድናቸውን ለማጠናከር በዝውውር መስኮቱ በንቃት እየተሳተፉ እንደሆነ ይታወቃል፡፡