Fana: At a Speed of Life!

ቱርክ፣ ሳኡዲ አረቢያ እና ፓኪስታን የጋራ ወታደራዊ ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ቱርክ፣ ሳኡዲ አረቢያ እና ፓኪስታን ራሳቸውን ከጥቃት መካለከልና ደህንነታቸውን ማስጠበቅ የሚያስችል የሶስትዮሽ ወታደራዊ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

የመካ ስምምነት የተሰኘውን የሦስቱ ሀገራት የወታደራዊ ትብብር ስምምነት የቱርኩ ፕሬዚዳንት ረሲብ ጣይብ ኤርዶኻን፣ የሳኡዲ ልኡል አልጋ ወራሽ ሞሀመድ ቢን ሰልማን እና የፓኪስታኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሻህባዝ ሻሪፍ ተፈራረመውታል፡፡

ስምምነቱ የሀገራቱን ወታደራዊ ትብብር የበለጠ ለማጠናከርና በመካከለኛው ምስራቅ እየተባባሰ በሚገኘው ውጥረት ውስጥ የሀገራቱን ደህንነት ለማስጠበቅ ያለመ መሆኑ ተመላክተዋል፡፡

ከሶስቱ በአንዱ ሀገር ላይ የተፈጸመ ማንኛውም ጥቃት በሌሎቹ ሀገራት ላይ እንደተፈፀመ ጥቃት ይቆጠራል የሚለው የጋራ ስምምነቱ፥ ሀገራቱ የደህንነት ስጋታቸውን በጋራ ለመከላከል ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ነው የተባለው፡፡

በተለይም በኢራን እንዲሁም በሁቲ ታጣቂዎች የሚሳኤል ጥቃት እየተፈፀመባት ለምትገኘው ሳኡዲ አረቢያ ከፍተኛ ወታደራዊ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ታምኖበታል፡፡

ፓኪስታን ለበርካታ ዓመታት ለሳኡዲ ወታደሮች የወታደራዊ ስልጠና እና የቴክኒክ ድጋፎችን ስታደርግ መቆየቷን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

በተመሳሳይ ቱርክ እና ፓኪስታን የጦር መርከቦችንና የስልጠና አውሮፕላኖችን ልውውጥ ሲያደርጉ መቆየታቸውን ያስታወሰው ዘገባው፥ በፈረንጆቹ 2023 ደግሞ ሪያድ የቱርክ ድሮኖችን ለመግዛት ስምምነት ፈፅማ እንደነበር ጠቅሷል፡፡

በሚኪያስ አየለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.