Fana: At a Speed of Life!

ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር በንግድና በደህንነት ዘርፎች ትብብሯን አጠናክራ ትቀጥላለች – ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር በንግድ፣ ኢንቨስትመንት እንዲሁም በጸጥታና ደህንነት ዘርፎች ያላትን ትብብር አጠናክራ ትቀጥላለች አሉ፡፡

ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር በመሆን ላለፉት አራት ዓመታት ላገለገሉት አምባሳደር ባጫ ደበሌ ሽኝት አድርገዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ በዚሁ ወቅት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ግንኙነት እያደገ መምጣቱን ጠቁመው፤ ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር በንግድ፣ ኢንቨስትመንትና በሀገራቱ የድንበር አካባቢ የጸጥታና ደህንነት ስራዎች ላይ ትብብሯን አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

በተጨማሪም በሁለቱ ሀገራት ዜጎች መካከል ያለውን የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት አጠናክሮ ለማስቀጠል መንግሥታቸው ቁርጠኛ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በሚኪያስ አየለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.