የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽንና ዳሽን ባንክ በፋይናንስ አቅርቦት በትብብር ለመስራት ተስማሙ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን እና ዳሽን ባንክ በጆይንት ቬንቸርና ኢንቨስትመንት የቤት ልማት ሥራዎች በፋይናንስ አቅርቦት ላይ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል፡፡
ስምምነቱን የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ረሻድ ከማል (ዶ/ር) እና የዳሽን ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አስፋው ዓለሙ ተፈራርመዋል፡፡
ኮርፖሬሽኑ ለሚያከናውነው ሰፊ የቤት ልማት መርሐ ግብር አስተማማኝ የፋይናንስ አቅርቦት ለመፍጠር ከሀገር ውስጥ የፋይናንስ ተቋማት ጋር ትብብሩን በማጠናከር ላይ እንደሚገኝ ተመላክቷል፡፡
በስምምነቱ መሠረት በጆይንት ቬንቸር አሰራር ስልት አዋጭ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ ለማድረግ ዳሽን ባንክ የፋይናንስ አማራጮችን ያቀርባል፡፡
ኮርፖሬሽኑ ለሚያከናውነው የቤት ልማት መርሐ ግብር የፋይናንስ አቅርቦት ከዳሽን ባንክ ለማግኘት ስምምነት ላይ መደረሱን የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡
በተጨማሪም በውጭ ምንዛሪ አቅርቦት ረገድ ተቋማቱ በትብብር ለመስራት መስማማታቸው ነው የተገለጸው፡፡