Fana: At a Speed of Life!

18ኛው የብሪክስ መሪዎች ጉባዔ በሕንድ ኒው ዴልሂ መካሄድ ጀመረ

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) 18ኛው የብሪክስ መሪዎች ጉባዔ በሕንድ ኒው ዴልሂ መካሄድ ጀምሯል።

በጉባዔው ላይ የብሪክስ አባል እና አጋር ሀገራት መሪዎች እና የዓለም አቀፍ ተቋማት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የሚሳተፉ ይሆናል።

የብሪክስ አባል ሀገር የሆነችው ኢትዮጵያም በጉባዔው ላይ ተሳትፎ እያደረገች ይገኛል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጉባዔው ላይ ለመሳተፍ ህንድ መግባታቸው ይታወቃል፡፡

መሪዎቹ በዓለም አቀፍ ደረጃ እያደገ የመጣውን የዲፕሎማሲ እና የኢኮኖሚ ትብብርን ይበልጥ ማጠናከር በሚያስችሉ አጀንዳዎች ላይ የሚመክሩ ይሆናል፡፡

የዘንድሮው ጉባኤ ዓለም አቀፍ አስተዳደርን ማጠናከር፣ በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት በዓለም አቀፍ ፖለቲካ ያላቸውን ተደማጭነትን ማሳደግ፣ የንግድና ኢንቨስትመንት አጋርነት ማጠናከር ላይ እንደሚያተኩር ይጠበቃል፡፡

ጉባዔው “ጽናትን፣ ፈጠራን፣ ትብብርን እና ዘላቂነትን መገንባት” በሚል መሪ ቃል ለሁለት ቀናት የሚካሄድ ይሆናል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.