Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በዚህ ሰሞን በርካታ ሀገራዊ ኢትዮጵያ በዚህ ሰሞን በርካታ ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸውን ተግባራት አከናውናለች- የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎትፋይዳ ያላቸውን ተግባራት አከናውናለች- የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በዚህ ሰሞን በፖለቲካ፤ በዲፕሎማሲ፤ በኢኮኖሚ እና በማህበራዊ ዘርፎች በርካታ ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸውን ተግባራት አከናውናለች አለ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት።

አገልግሎቱ ኢትዮጵያ በዚህ ሰሞን በሚል በቪዲዮ ባጋራው መልዕክት፥ በዚህ ሰሞን ኢትዮጵያ በፖለቲካ፤ በዲፕሎማሲ፤ በኢኮኖሚ እና በማህበራዊ ዘርፎች በርካታ ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸውን ተግባራት አከናውናለች ብሏል።

እነዚህ ክንውኖች የሀገሪቱን የልማት ጉዞ ማጠናከር፤ የወጣቶችን ተሳትፎ ማሳደግ፤ የመሠረተ ልማት ማስፋፋት እና የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ ተሳትፎ ማጎልበት ላይ ያተኮሩ ናቸው ሲልም አብራርቷል።

የአገልግሎቱ ሙሉ መልዕክት እንደሚከተለው ቀርቧል ፥

ኢትዮጵያ በዚህ ሰሞን በፖለቲካ ዘርፍ

👉ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመትን አስመልክተው ማዕድ አጋርተዋል።

👉ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተሳተፉበት የ18ኛው የብሪክስ ጉባኤ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅሞች ለመላው ዓለም ማስገንዘብ ተችሏል።

👉ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከጉባኤው ጎን ለጎን ከሕንድ፣ ሩሲያ፣ ቻይና፣ UAE፣ ካዛኪስታን፣ ማሌዢያ፣ ቬትናም እና ኢራን መሪዎች ጋር ፍሬያማ ውይይት አድርገዋል።

👉በሞጆ በ60 ሄክታር መሬት ላይ የተገነባውን ዘመናዊ የሎጀስቲክስ ማዕከል ማስፋፊያ የመጀመሪያ ምዕራፍ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል።

👉አቶ ክርስቲያን ታደለን ጨምሮ ከ600 በላይ እስረኞች በይቅርታና ክሳቸው ተቋርጦ ከእስር እንዲለቀቁ ተደርጓል።

👉የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ “2019 ዓ.ም የመከላከያ ሠራዊታችን አቅም የበለጠ የሚጠናከርበት ዓመት ይሆናል” ሲሉ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ በዚህ ሰሞን በዲፕሎማሲ ዘርፍ

👉ኢትዮጵያ በ18ኛው የብሪክስ ጉባኤ ያሳየችው ንቁ ተሳትፎ እና የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ንግግር የሀገሪቱን ስትራቴጂካዊ ጥቅም ያስከበረና የአፍሪካን ድምፅ ከፍ ያደረገ አዲስ የውጭ ፖሊሲ ምዕራፍ ተደርጎ ተወስዷል።

👉በጂቡቲ በተካሄደው 74ኛው የኢጋድ (IGAD) ሚኒስትሮች ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የቀጣናው ሀገራት ተወካዮች በንቃት ተሳትፈዋል።

👉የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ ማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም የሚያደርገውን ድጋፍ የሚያጠናክር መሆኑን አረጋገጠ።

👉እስራኤል ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ታሪካዊ ግንኙነት በኢንቨስትመንት፤ ቴክኖሎጂና ሰው ሀብት ልማት ወደ ላቀ አጋርነት መሸጋገሩን በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አሳወቁ።

👉ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ የኳታር ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ አቀረቡ።

👉በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች ለኢትዮጵያ መንግሥት እና ሕዝብ የዘመን መለወጫ እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላላፈዋል።

👉ኢትዮጵያን ጨምሮ 181 አባል ሀገራት የተሳተፉበት የዓለም አቀፍ የአቶሚክ ኤነርጂ ኤጀንሲ (IAEA) 70ኛ አጠቃላይ ጉባኤ በቪየና፤ ኦስትሪያ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

👉በአሜሪካ ይገኙ የነበሩ 17 ጥንታዊ የብራና መጻሕፍት ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

ኢትዮጵያ በዚህ ሰሞን በኢኮኖሚ ዘርፍ

👉የቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት እ.ኤ.አ. በ2026 በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የበረራ እና የቱሪስት ትስስር ካላቸው 50 ዓለም አቀፍ ኤርፖርቶች አንዱ በመሆን ተመርጧል።

👉ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ያደነቀ ሲሆን፤ በተለይም የውጭ ምንዛሪ ገበያ በፍላጎትና አቅርቦት መመራቱና የዋጋ ንረትን ለመቀነስ የተወሰዱ እርምጃዎች አዎንታዊ ሚና ማበርከታቸው ተገልጿል።

👉በሀገራችን የመጀመሪያውን የተለየ የቤት መግዣ ብድር መልሶ ማጠናከሪያ ኩባንያ ለማቋቋም የሚያስችል የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና በ IFC መካከል ተፈጽሟል።

👉ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦቱን ከአጥፍ በላይ በማሳደግ ሀገሪቱን የቀጣናው ዋና የኃይል አስተሳሳሪ አድርጓታል።

👉የሀገር ውስጥ የቴምር ምርትን በማሳደግ ለምርት ማስገቢያ ይወጣ የነበረውን ከ9 ሚሊየን ዶላር በላይ ማዳን ተችሏል።

ኢትዮጵያ በዚህ ሰሞን በኢኮኖሚ ዘርፍ

👉የኢትዮጵያ አየር መንገድም ለ9ኛ ጊዜ “የአፍሪካ ምርጥ አየር መንገድ” በመባል ተሸልሟል።

👉የአውሮፓ ኅብረት እና አባል ሀገራት ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ሪፎርም እና አካታች ልማት የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።

👉በ2018 በጀት ዓመት 860 አዳዲስ የቱሪስት መስህቦች የለሙ ሲሆን፤ እንደ ላሊበላ፤ ፋሲል ግቢ፤ ሐረር ጀጎልና ሶፍ ኡመር ያሉ ታሪካዊ ቅርሶች ታድሰው ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል።

👉የመስቀል እና የእሬቻ በዓላትን ምክንያት በማድረግ በርካታ የውጭ ሀገር ቱሪስቶችና ዳያስፖራዎች ወደ ሀገር ውስጥ እየገቡ ይገኛሉ።

ኢትዮጵያ በዚህ ሰሞን በማህበራዊ ዘርፍ

👉የተቀናጀ የአፈርና ውኃ ጥበቃ እንዲሁም የአረንጓዴ ዐሻራ ዘመቻ 38 ሚሊየን ሄክታር የተጎሳቆለ መሬት እንዲያገግም ያደረገ ሲሆን፤ ከ2011 እስከ 2018 ዓ.ም ድረስ 56 ቢሊየን ችግኞች ተተክለዋል።

👉አዲስ አበባ ያጋጠሟትን አደጋዎች የመቋቋም አቅሟ በዓለም አቀፍ “Alpha Geo” ተቋም ተመዝኖ ከአፍሪካ 1ኛ፤ ከዓለም 2ኛ ደረጃን ይዛለች።

👉ከሳዑዲ ዓረቢያ 1 ሺህ 861 ኢትዮጵያውያን የተመለሱ ሲሆን፤ ባለፈው አንድ ዓመት የተመለሱት ከ101 ሺህ 800 በላይ ደርሰዋል።

👉ኢትዮጵያ ለድንገተኛ የሕዝብ ጤና አደጋዎች ለምትሰጠው ምላሽ ከዓለም ጤና ድርጅት (WHO) እውቅና አግኝታለች።

👉ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለአዲሱ ትምህርት ዘመን ለተማሪዎች የስኬት ምኞት ያስተላላፉ ሲሆን የትምህርት ሚኒስቴር የቀብሪደሀር ዩኒቨርሲቲ የፔትሮሊየም እና ተፈጥሮ ጋዝ ልዩ የልህቀት ማዕከል አድርጎ ሰይሟል።

👉በአጠቃላይ በዚህ ሰሞን የተከናወኑ ተግባራት በሀገራዊ ልማት፤ በዜጎች ተጠቃሚነት፤ በዲጂታል ሽግግር እና በዓለም አቀፍ ትብብር ዘርፎች የሚታዩ እድገቶችን ያሳያሉ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.