Fana: At a Speed of Life!

ጊፋታ ወንደማማችነትን የሚያጠናክር በዓል ነው – አቶ ጥላሁን ከበደ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የወላይታ ህዝብ የዘመን መለወጫ የጊፋታ በዓል ወንደማማችነትን የሚያጠናክር በዓል ነው አሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ።

የወላይታ ብሔር ዘመን መለወጫ “ጊፋታ” በወላይታ ሶዶ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው።

በዚሁ ወቅት ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ፥ በዩኔስኮ የማይዳሰሱ ቅርሶች የተመዘገበው ጊፋታ በሀገር ደረጃ እርስ በእርስ የሚደጋገፍ ህዝብ ለመፍጠር ትልቅ ሚና አለው ብለዋል።

የጊፋታ በዓል ውብ በሆኑ ልዩ ልዩ ባህሎች የሚደምቅ የክልሉ ፣ የሃገር ብሎም የዓለም ሀብት ነውና በየጊዜው አከባበሩን በማድመቅ ለዓለም ማሳየት የሁሉም ተቀዳሚ ሃላፊነት ሊሆን ይገባል ነው ያሉት።

የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሳሙኤል ተሰማ በበኩላቸው ጊፋታ የህዝቦች አብሮነት ማሳያ መሆኑን ጠቅሰው በዓሉን በጋራ ለማክበር ከተለያዩ ሀገራት የመጡ እንግዶችን አመስግነዋል።

የዘንድሮው የጊፋታ በዓል የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር በስኬት ከተጠናቀቀ በኋላ የሚከበር በመሆኑ ልዩ ያደርገዋል ያሉት ደግሞ የወላይታ ሶዶ ከተማ ከንቲባ እታገኝ ኃ/ማርያም ናቸው።

በጥላሁን ሁሴን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.