ደረጃቸውን የጠበቁ የኤሌክትሪክ እቃዎችን ለውጭ ገበያ ለማቅረብ እየሰራሁ ነው አለ ሮሜል ኤሌክትሪካል
አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኤሌክትሪክ እቃዎችን ጥራት በማሳደግ ከሀገር ውስጥ አቅርቦት በተጨማሪ ወደ ውጪ ገበያ ለማቅረብ በቁርጠኝነት እየሰራሁ ነው አለ ሮሜል ኤሌክትሪካል፡፡
በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ማምረትና አቅርቦት ዘርፍ አስተማማኝ ጥራትንና የገበያ መሪነትን ያረጋገጠው ሮሜል ኤሌክትሪካል አዳዲስ እና ዘመናዊ ምርቶቹን ይፋ አድርጓል፡፡
መርሐ ግብሩ በዋነኝነት “ጥራት የመጨረሻው መዳረሻችን ሳይሆን የማንደራደርበት መነሻችን ነው” በሚለው የድርጅቱ መርህ ላይ ያተኮረ ነው፡፡
የሮሜል ኤሌክትሪካል ቺፍ ማርኬቲንግ እና ሺያጭ ኦፊሰር የሮሜል ደንበኞች የረጅም ዓመት አብሮነት ጉዞ እና የሮሜል አካል በመሆን በሀገራችን ቀዳሚ ብራንድ እንዲሆን ላበረከቱት ጉልህ አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ድርጅቱ በኢትዮጵያ የሚያደርገውን ኢንቨስትመንት በማሳደግ ከደንበኞች ጋር ያለውን የረጅም ጊዜ አጋርነት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡
በተጨማሪም ሮሜል በቀጣይ ከሀገር ውስጥ አቅርቦት በተጨማሪም ወደ ውጪ ገበያም ለማቅረብ በሰፊው እየሰራ እንደሚገኝ ነው ያመላከቱት፡፡
በዕለቱ የፋብሪካው ሥራ አስኪያጅ በበኩላቸው ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የደህንነትና የጥራት መመዘኛዎችን ያሟሉ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ለደንበኞች ይፋ አድርገዋል፡፡
በገበያው ላይ ይፋ ከተደረጉት ዘመናዊ ምርቶች መካከል የሮሜል ፒያኖ ሲሪየስ ስዊቾች እና ሶኬቶች፣ ብሬከሮች፣ ማግኔቲክ ትራክ ላይቶች፣ ሊኒየር ላይቶች፣ የሮሜል ኬብል ትራንኪንግ፣ የሮሜል ዋተር ፕሩፍ ሲሊንግ ላይት እና የሮሜል ዲስትሪቢዩሽን ቦርዶች ይገኙበታል፡፡
በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙ እንግዶች በዋና መሥሪያ ቤቱ የሚገኙ ዘመናዊ ሾውሩሞችን የጎበኙ ሲሆን፣ በሀገር ውስጥ የሚመረቱትን የኤሌክትሪክ ውጤቶች እንዲሁም ከውጭ የሚገቡትን ዘመናዊና ቅንጡ መብራቶች ተመልክተዋል።
ሮሜል ኤሌክትሪካል በሀገሪቱ ያለውን የኤሌክትሪክ ምርቶች ለማዘመንና በጥራትም ከፍ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጧል።
ሮሜል ኤሌክትሪካል በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች አምራችና አቅራቢ ድርጅት ሲሆን፣ ከ20 ዓመታት በላይ ለኢንዱስትሪ፣ ለንግድና ለመኖሪያ ቤቶች የሚሆኑ ጥራታቸው የተረጋገጡ የኤሌክትሪክ ምርቶችን በማቅረብ በገበያው ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ነው።