Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ለመስቀል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለመስቀል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያስተላለፉት መልዕክት ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፦

ለመስቀል በዓል እንኳን አደረሳችሁ

የመስቀል በዓል ሃይማኖታዊና ባህላዊ በሆነ መንገድ በመላው ኢትዮጵያ የሚከበር በዓል ነው።

በዓሉ ቤተሰባዊ እና ማኅበራዊ ቀለም አለው። ቤተሰብ ይገናኝበታል። ሠፈሩ ይሰባሰብበታል። ከተማውና አካባቢው ወደ አንድ አደባባይ ይተምበታል።

ከእንጨት እስከ ደመራ ያለው መሰባሰብም የመደመርን ኃይል የሚያሳይ ተምሳሌት ነው።

በዓሉን በምናከብርበት ጊዜ ሁሉ የኢትዮጵያን ዐቅሞች እያሰባሰብንና እየደመርን ታላቅ ሀገራዊ ዐቅም ለመፍጠር እንትጋ።

በድጋሚ መልካም በዓል ይሁን።

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!

ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!

መስከረም 16፣ 2019 ዓ.ም

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.