Fana: At a Speed of Life!

ጋሪ ዎሮ በውስጡ የያዘውን የአብሮነትና የፍቅር እሴት ለትውልድ ግንባታ መጠቀም ይገባል – ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ጋሪ ዎሮ በውስጡ የያዘውን የአብሮነትና የፍቅር እሴት ለትውልድ ግንባታ፣ ለዘላቂ ሰላም እና ልማት መጠቀም ይገባል አሉ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን፡፡

የቦሮ ሽናሻ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ “ጋሪ ዎሮ” በአሶሳ ከተማ የቤኒሻንጉል ጉመዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰንን ጨምሮ የተለያዩ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት እየተከበረ ነው፡፡

ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን በዚሁ ወቅት እንዳሉት÷ በክልሉ ለባህል ልማት መሠረት የሚጥሉ ሥራዎች እየተሠሩ ይገኛሉ፡፡

በአሶሳ ከተማ የተጀመረው የባህል ማዕከል ጋሪ ዎሮን ጨምሮ ለብሔረሰቡ ባህላዊ እሴቶች ልማት ትልቅ ፋይዳ ያለው በመሆኑ ሁሉም ድጋፍ ሊያደርግ ይገባል ብለዋል።

ክልሉ በብዝኃ ባህል የታደለ መሆኑን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ መንግሥት እነዚህን ባህላዊ እሴቶች በማልማት ለቀጣዩ ትውልድ እንዲተላለፉ እየሠራ የሚገኘውን ሥራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

ጋሪ ዎሮ በውስጡ የያዘውን የአብሮነትና የፍቅር እሴት ለትውልድ ግንባታ፣ ለዘላቂ ሰላም እና ልማት መጠቀምይገባል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ መረጃ አመላክቷ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.