Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል የሕዝቡን ተጠቃሚነት ይበልጥ ማሳደግ የሚያስችል አደረጃጀት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ጨፌ ኦሮሚያ እያካሄደ ባለው 1ኛ ዓመት 7ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባዔው የቀረበለትን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አስፈጻሚ አካላት የማቋቋሚያ አዋጅ አጽድቋል።

በጉዳዩ ላይ መግለጫ የሰጡት የክልሉ ፍትሕ ቢሮ ሃላፊ አቶ ጉዮ ዋሪዮ እንዳሉት÷ ጨፌ ኦሮሚያ የሕዝቦችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ታሪካዊ ውሳኔ ማሳለፉን ጠቅሰዋል።

ዛሬ በጨፌው የጸደቀው የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አስፈጻሚ አካላት አዋጅ ረቂቅ የመንግሥት አካላትን ቅንጅት የሚያጠናክር መሆኑን ተናግረዋል።

ሪፎርሙ በሕግ የተደገፈና ሥልጣንን ወደ ታች ለማውረድ ያለመ መሆኑን ጠቁመው÷ ቀደም ሲል 21 የነበሩት ዞኖች ወደ 6 ዞኖች መዋቀራቸውን አስረድተዋል።

እነዚህ ዞኖችም፦

1. የኦሮሚያ ምስራቅ ዞን
2. የኦሮሚያ ማዕከላዊ ዞን
3. የኦሮሚያ ምዕራብ ዞን
4. የኦሮሚያ ደቡብ ዞን
5. የኦሮሚያ ደቡብ ምዕራብ ዞን
6. የኦሮሚያ ደቡብ ምስራቅ ዞን መሆናቸውን ገልጸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.