ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ተጋሪ ሀገር እንድትሆን የሚያስችላት ህጋዊ መብት አላት-ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ)ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ተጋሪ ሀገር እንድትሆን የሚያስችላት ህጋዊ መብት አላት አሉ የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ፡፡
ፕሬዚዳንቱ ከአል አራቢያ ጋር ባደረጉት ቆይታ ÷ኢትዮጵያ የባህር በር የሌላት ሀገር መሆኗን ጠቅሰው
በቀጥታ ከቀይ ባህር ጋር ባትዋሰንም የቀይ ባህር ተጋሪ ሀገር እንድትሆን የሚያስችላት ህጋዊ መብት አላት ብለዋል፡፡
በመሆኑም በአለም አቀፍ የውሃ ህጎች መሰረት ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ተጋሪ ሀገር ልትሆን ይገባል ነው ያሉት፡፡