Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአዲሱ የመደመር መንግሥት ምሥረታ እና የኢፌዴሪ 7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመስረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፦

👉 ዛሬ ከተማና ገጠሩ እየተቀየረ ነው፤
👉 ከተሞቻችን የዘመናዊ ከተማ መልክ ለመያዝ ጥረት ማድረግ ጀምረዋል፤
👉 ዛሬ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ውብ አበባ ተብላ ብትጠራ እውነታ እንጂ ሙገሳ ተደርጎ አይወሰድም፤
👉 መሶብ የኢትዮጵያን የአገልግሎት አሰጣጥ መልክ ሲያስተካክለው፤ ፋይዳ አዲሱን የዲጂታል ማንነት ሲያጠናክረው፤
የወንዝ ዳር ልማት የኢትዮጵያን የውኃ እሳቤ ሲቀይረው፤ የገበታ ፕሮጀክት የኢትዮጵያን ነባር መልኮች በአዲስ መልክ ሲገልጡ በዓይናችን አይተናል፡፡
👉 የአዲስ አበባ ለውጥ የዓለም ጉባኤዎችን ኑ ወደኔ እያለ ሲጣራ፤ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የምርት ባህላችንን ሲያድሰው፤ የማዕድን ልማታችን ለዘመናት የወጪ ንግዳችንን በአጭር ጊዜ መብለጥ ሲችል ለመታዘብ በቅተናል፡፡
👉 እነዚህን ተስፋ ሰጪ ጅማሮዎች አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡
👉 ባለፉት ዓመታት የመጣንበት መንገድ እንደ ኮሪደር የተስተካከለ፤ እንደ ወንዝ ዳር ልማት ያማረ አልነበረም ብዙ ፈተናዎችን አልፈናል፡፡
👉 የኢትዮጵያ ለውጥ ያስደነገጣቸው አካላት በክፉ አይናቸው ያዩን ጀመር፡፡
👉 የችግኝ ዋርካ ከሆነች አንችላትም ብለው ሰጉ፤ ስለዚህ ባልበላው ጭሬ አፈሰዋለው በሚለው ደካማ መንገድ ተነሱ፡፡
👉 ከሮጠች አንይዛትም ብለው የመጨረሻውን ጥይታቸውን መተኮስ ጀመሩ፡፡
👉 ባዳና ባንዳ ለእኩይ ዓላማ ተባበሩ፤ ሀገር ሻጭና ሀገር በታኝ ቀብድ ተቀባበሉ፡፡
👉 በሰይፍም በሰልፍም፤ በውሸትም በሀሜትም፤ በተንኮልም በሽረባም ባገኙት የትግል ሜዳ ሁሉ ከጉዟችን ሊያደናቅፉን መከራቸውን አዩ፤ ኢትዮጵያን ግን አልቻሏትም፤ አይችሏትም፡፡
በመልካም ፈቃዱ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.