Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሞችን ማስጠበቅ የሚያስገኘው ትርፍ እጅግ ብዙ ነው -ፕሬዚዳንት ታዬ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሞችን ማስጠበቅ የሚያስገኘው ትርፍ እጅግ ብዙ ነው አሉ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ።
ፕሬዚዳንቱ በኤክስ ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሞችን በዘላቂነት ለማስጠበቅ ከአድማስ ባሻገር ማሰብ እና ደፋር ስትራቴጂካዊ አመለካከት ማዳበር ይገባል ብለዋል።
አክለውም የወደፊቱን መተንበይ እና ሀገርን ከፍ ለማድረግ በጽኑ የቆሙ ደፋር ስትራቴጂካዊ አመለካከቶችን ማዳበር ወሳኝ ነው ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል።
ፕሬዚዳንቱ እንዲህ ዓይነት የነገ አሻጋሪ እና አርቆ አሳቢ አቀራረብ መከተል ሀገሪቱ ለምታስመዘግበው ሁለንተናዊ ድልና ስኬት የሚያስገኘው ጥቅም እጅግ የላቀና ብዙ መሆኑን አስገንዝበዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.