Fana: At a Speed of Life!

የታንዛኒያ ፕሬዚዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የታንዛኒያ ፕሬዚዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያን ለመምራት በድጋሚ በመመረጣቸው የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ፕሬዚዳንቷ በመልዕክታቸው÷ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በድጋሚ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመሰየምዎ በታንዛኒያ ሕዝብ እና መንግሥት ስም እንኳን ደስ አለዎት ብለዋል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ድጋሚ መመረጥ ላሳዩት የአመራር ጥበብ እና ለኢትዮጵያ እድገት ላላቸው ራዕይ የተሰጠ መተማመኛ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ታንዛኒያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ዘርፈ ብዙ ግንኙነት ታከብራለች ያሉት ፕሬዚዳንቷ ÷ መንግሥታቸው ከኢትዮጵያ ጋር በሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት፣ በጋራ እና በቀጣናዊ ፍላጎቶች ዙሪያ በትብብር መስራቱን እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.