Fana: At a Speed of Life!

ወጥ የሆነ ሀገራዊ የህግ አተገባበርና አተረጓጎም እንዲኖር የሚያስችል ጉባኤ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ወጥ የሆነ ሀገራዊ የህግ አተገባበርና አተረጓጎም እንዲኖር የሚያስችል ጉባኤ በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ቴዎድሮስ ምህረት በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ የማኅበረሰቡን እርካታ ለማረጋገጥ በጉባኤው የተገኙ ውጤቶችን በማጽናት በአፈጻጸም ሂደት ያጋጠሙ ጉድለቶችን ማረም አስፈላጊ ነው፡፡
ጉባኤው ወጥ የሆነ ሃገራዊ የሕግ አተገባበርና አተረጓጎም እንዲኖር ማስቻልን ዓላማው ያደረገ ነው ብለዋል፡፡
ጉባኤው የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች የለውጥ ፍኖተ ካርታ አተገባበርን በመገምገም ሁሉም ፍርድ ቤቶች ካላቸው ነባራዊ ሁኔታ በመነሳት ወጥ አተገባበር እንዲኖር ለማስቻል እንደሚመክር ነው ተገለጸው።
የማኅበረሰቡን እርካታ ለማረጋገጥ በጉባኤው የተገኙ ውጤቶችን በማጽናት በአፈጻጸም ሂደት ያጋጠሙ ጉድለቶችን ማረም አስፈላጊ ነው ሲሉ አሳስበዋል።
በለውጥ አተገባበር ሂደቱ የፍርድ ቤቶች የዲጂታላይዜሽን ሥራ ያለበትን ደረጃ ከመመርመር በተጨማሪ የፍርድ ቤቶች የተቀናጀ የመረጃ ፍሰት ቴክኖሎጂ፣ የቨርቹዋል የፍርድ ቤት አገልግሎቶች፣ የኢ-ፋይሊንግና ሌሎች አገልግሎቶችን ማስፋፋትን የተመለከቱ ጉዳዮች ትኩረት ተሰጥቷቸዋል ብለዋል።
ይህ ጉባኤው በቀጣይ ሶስት ዓመታት የሚተገበር የለውጥ ፍኖተ ካርታን እንደሚያፀድቅና የአፈጻጸም ሥርዓቱን አስመልክቶም የክትትል ሥርዓት እንደሚያዘጋጅ ይጠበቃል።
በደሳለኝ ቢራራ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.