Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት 99 ነጥብ 6 በመቶ የተገልጋይ እርካታ ተመዝግቧል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ በመሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግሥት አግልግሎት ፈጣንና ተደራሽ አገልግሎት በመስጠት 99 ነጥብ 6 በመቶ የተገልጋይ እርካታ ተመዝግቧል አለ የከተማዋ ከንቲባ ጽ/ቤት።

ጽ/ቤቱ ፥ የከተማ አስተዳደራችን የህዝብ ተሳትፎንና ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረገ ቀልጣፋ አስተዳደር በመዘርጋት፣ የነዋሪዎቿን ሁለንተናዊና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በበጀት ዓመቱ አንደኛ ሩብ ዓመት ጠንካራ የተቋም ግንባታን ቁልፍ ስራ አድርጎ በመስራት ውጤቶች ተመዝግበዋል ብሏል።

በዚህም በመሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግሥት አግልግሎት ፈጣንና ተደራሽ አገልግሎት በመስጠት 99 ነጥብ 6 በመቶ የተገልጋይ እርካታ ማስመዝገብ መቻሉን አመልክቷል።

የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዋና መስሪያ ቤቱን ጨምሮ በ11ም ክፍለ ከተሞች ቀልጣፋ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

ከዚህ ቀደም ዲጂታል የተደረጉ 392 አገልግሎቶች የማጥራት ስራ ተሰርቶባቸው ስራ ላይ የዋሉ ሲሆን፤ ተጨማሪ 324 አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል ስርዓቱ ለማስገባት ተለይተዋል።

ከእነዚህም ውስጥ በሩብ ዓመቱ ትግበራ ይጀምራሉ ከተባሉት 30 ዋና ዋና አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ ገብተዋል።

በተጨማሪም የአገልግሎት ጥራትን ለማረጋገጥ በ78 ተቋማት ላይ የክትትልና ድጋፍ ስራ ተሰርቶ፤ በተገኙ ክፍተቶች ላይ የማስተካከያ ግብረ-መልስ እየተሰጠ ይገኛል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.