Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ 19ኛው ሠንደቅ ዓላማ ቀንን አስመልክቶ ያስተላለፉት መልዕክት ዋና ዋና ነጥቦች፡-

👉 የአንድነትና የሉዓላዊነት ክብራችን ኃያል መገለጫ በሆነው ሠንደቅ ዓላማችን ስር ተሰባስበን ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን በሚል መሪ ቃል ለምናከብረው 19ኛው የሠንደቅ ዓላማ ቀን እንኳን አደረሳችሁ፤
👉 እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ለሀገሩ ያለውን ፍቅር፣ ክብርና ቃልኪዳን በልቡ የሚያድስበት ህብረብሔራዊ ኢትዮጵያዊነትን በጋራ የምናጎለብትበት የነገውን ብሩህ ተስፋችንን የምናበረታበት ታላቅ ብሔራዊ ዕለት ነው፤
👉 ሠንደቅ ዓላማችን የብሔራዊ ህብረታችንና አንድነታችን ማሳያ፣ የዜጎች ሀገራዊ ፍቅርና ሀገራዊ ስሜት መገለጫ ታሪካዊ ማህበራዊ ትስስራችንን እና የስነልቦና አንድነታችንን ማጽኛ ምልክታችን ነው፤
👉 ሠንደቅ ዓላማ የመስዕዋትነት፣ የነጻነት፣ ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነታችን መለኪያ፤ የሕዝቦች እኩልነትና የህብረታችን ህያው ምስክር ነው፤
👉 ጀግኖች ኢትዮጵያውያን ደምና አጥንታቸውን ከስክሰው ውድ የህይወት መስእዋትነት ከፍለው በክብር ያስረከቡን ነው፤
👉 ሠንደቅ ዓላማችን በልባችን ታትሞ የቆየ የአሸናፊነትና የነጻነታችን ዓርማ ነው፤
👉 ሀገራችን ኢትዮጵያ ለብዙ ሺህ ዓመታት ነጻነትና ሉዓላዊነቷን አስጠብቃ ታፍራና ተከብራ የቆየች ታላቅ ሀገር ስትሆን፤ የሠንደቅ ዓላማ ታሪኳም እንዲሁ አብሮ ከሀገረ መንግሥት ግንባታዋ ጋር በእጅጉ የተቆራኘና የተሳሰረ ነው፤
👉 የኢትዮጵያ ሠንደቅ ዓላማ በእኛ ብቻ ሳይሆን በመላው የጥቁር ህዝቦችና በአፍሪካውያን ዘንድ የነጻነት፤ የእኩልነትና የጽናት ተምሳሌት በመሆኑ በርካታ ሀገራት ቀለማቱን የነጻነታቸው ዓርማ አድርገው ወስደውታል፤
👉 እነዚህ ሀገራትና ህዝቦች ተምሳሌታችንን ስለወረሱ ከፍ ያለ ምስጋና ለማቅረብ እሻለሁ፤
👉 ኢትዮጵያችን የባለ ብዙ መልክ ባህሎች፣ ቋንቋዎች፣ ሀይማኖቶች እንዲሁም በርካታ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ሀብቶች ሀገር ናት፤
👉 ብዙ ሆና አንድ፤ አንድ ሆና ደግሞ ብዙ ነች፤ የዚህ ሁሉ ውበትና የህብረብሔራዊ ጥንካሬ መገለጫ ደግሞ ይሄው ብሔራዊ ሠንደቅ ዓላማችን ነው፡፡
👉 ሀገራችን በቅርብ ዓመታት የገጠሟትን ከባድ የህልውና ፈተናዎች በህዝቦቿ የተባበረ ክንድ በፅናት ተሻግራ የራሷን ዕድል የመወሰን ብቃቷን እያስመሰከረች ትገኛለች፡፡
በመልካም ፈቃዱ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.