Fana: At a Speed of Life!

ቀዳማይ ልጅነት ላይ በትኩረት መስራት ጤናማና ኃላፊነት የሚሰማው ትውልድ ለመገንባት ወሳኝ ነው – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ቀዳማይ ልጅነት ላይ በትኩረት መስራት ጤናማ፤ ብቁና ኃላፊነት የሚሰማው ትውልድ ለመገንባት ወሳኝ ነው አሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፡፡
የአፍሪካ ከተሞች የከንቲባዎች ፎረም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ መንግሥት የከተማዋን የመሠረተ ልማት ስራዎች ከሕጻናት እድገትና ደህንነት ጋር በማስተሳሰር እየሰራ ነው፡፡
አዲስ አበባ ለመጪው ትውልድ ምቹ ሆና እየተገነባች ያለች የአፍሪካውያን ከተማ መሆኗን አንስተው፤ የራሷን ገቢ በተገቢው መንገድ መሰብሰብ መቻሏ እና በየዓመቱ ገቢ የመሰብሰብ አቅሟ በ50 በመቶ እየጨመረ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
አፍሪካውያን መሪዎች እርስ በርስ ልምድ በመካፈል የከተሞቻቸውን ለውጥ በማፋጠን ለዜጎችቻቸው ምቹ የሆኑ ከተሞችን መፍጠር እንደሚገባቸውም አጽንኦት ሰጥተዋል።
በፎረሙ ላይ ከ55 በላይ የአፍሪካ እንዲሁም ከ15 በላይ የሀገር ውስጥ ከተሞች ከንቲባዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡
በተካልኝ ኃይሉ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.