የኢትዮጵያ አየር መንገድና የቻይና ሳውዘርን አየር መንገድ ትስስራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ
አዲስ አበባ፣ጥቅምት4፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድና ቻይና ሳውዘርን አየር መንገድ በአፍሪካና ቻይና መካከል ያለውን የአየር ትራንስፖርት ትስስር ለማጠናከር የሚያስችል የጋራ ስምምነት ተፈራርመዋል።
ስምምነቱ ተጓዦች በሁለቱ አየር መንገዶች አማካይነት በአፍሪካና ቻይና የተለያዩ መዳረሻዎች መካከል በቀላሉ እንዲጓዙ የሚያስችል እንደሆነ የአየር መንገዱ መረጃ ያመላክታል።