Fana: At a Speed of Life!

የአኗኗር ዘይቤ ማሻሻልን ከምርታማነት ማሳደግ ጋር ያስተሳሰረው የመደመር ዕሳቤ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የመደመር መንግሥት የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመን በወሰደው ርምጃ ተጨባጭ ውጤት ተመዝግቧል።

ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋምና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የምታደርገውን ጥረት በማጠናከር የግብርና ምርታማነት በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል።

በግብርናው ዘርፍ እያስመዘገበች ካለው ከፍተኛ እመርታ ባሻገር በአረንጓዴ አሻራ ልማትም የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም የሚያስችል ከፍተኛ ስራ ሰርታለች። ይህም የግብርና ምርታማነትን የማሳደግ ጥረቱን እየደገፈ ይገኛል።

ከዚህ ቀደም ሀገሪቱ ከውጭ ታስገባቸው የነበሩ እንደ ስንዴ፣ ሩዝ፣ አትክልትና ፍራፍሬ የመሳሰሉ የግብርና ምርቶች ላይ መሰረታዊ ለውጥ በማምጣት እና ምርታማነትን በማሳደግ ወደ ውጭ መላክ የቻለችበትን ስኬት አስመዝግባለች።

በግብርና ዘርፍ የተገኘው አመርቂ ስራ በአፍሪካ ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ በልዩነት የሚታይ ሲሆን፤ ብዙዎቹ ተሞክሮዋን መውሰድ ጀምረዋል።

በመደመር መንግሥት ዕይታ ግብርናን ጨምሮ በየዘርፎቹ የተመዘገበውን እመርታ አጠናክሮ ለማስቀጠል አሁንም ትኩረት ተሰጥቷል። ምርታማነትን ከማሳደግ ባሻገር የህብረተሰቡን የአኗኗር ዘይቤም ትኩረት አግኝቷል።

የግብርና ትራንስፎርሜሽንን ለማረጋገጥ የግብርና ምርቶች ላይ እሴት በመጨመር ዘርፉን ገበያ መር ለማድረግ እየተሰራ ነው። የገጠር ትራንስፎርሜሽንን እውን ለማድረግ የአካባቢን ሀብት መሰረት ያደረገ ልማት አየተከናወነ ነው።

አርሶ አደሩን ከዝናብ ጥገኝነት በማላቀቅ ምርታማነትን ማሳደግ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶታል።  ያለውን የውሃ አማራጭ ለመጠቀም አነስተኛ የመስኖ ልማትን ጨምሮ የተለያዩ ተግባራት በመከናወን ላይ ናቸው። ከዚሁ ጎን ለጎን አርሶና አርብቶ አደሩ ኑሮው እንዲዘምን እና እንዲሻሻል እየተሰራ ነው።

የገጠር ትራንስፎርሜሽንን ለማረጋገጥ የግብርና ሽግግር፣ የመሰረተ ልማት እና ማህበራዊ ልማትን በመገንባት የገጠር መሰረተ ልማቶችን በማሟላት የማህበረሰቡ ተጠቃሚነት ማሳደግ ተችሏል።

የገጠሩን ማኅበረሰብ የኑሮ ደረጃ ማሻሻል፣ የኢኮኖሚ ትስስርን ማጠናከር፣ ቀጣይነት ያለው ልማትን ማረጋገጥ እና ሌሎች ዓላማ የያዘው የገጠር ኮሪደር ልማት፤ የአርሶና አርብቶ አደሩን የአኗኗር ዘይቤ አዘምኗል።

እንደ ሶላርና ባዮጋዝ ያሉ አኗኗርን የሚያቀልሉ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም የሚያስችል መሠረተ ልማቶችን ያካተቱ ሞዴል መንደሮችን በተለያዩ ክልሎች በስፋት መገንባት ጀምረዋል።

 

#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.