Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ34 ቢሊየን ብር በላይ ሃብት ማዳን ተቻለ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8 ፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ34 ቢሊየን ብር በላይ ሃብት ማዳን ተችሏል አለ የክልሉ ሴቶች፣ ወጣቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ፡፡

ቢሮው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማጠቃለያ እና የበጋ በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር አካሂዷል።

በመድረኩ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ይርጋ ሲሣይ እንዳሉት÷ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍሎችን በማነቃነቅ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያላቸው የበጎ ፈቃድ ሥራዎች ተከናውነዋል።

በዚህም በመንግሥት እና በልማት ድርጅቶች የማይሸፈኑ ሥራዎችን በመሥራት የበጀት ክፍተቶችን መሙላት ተችሏል ነው ያሉት፡፡

የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራ በክረምት ብቻ መቆም የለበትም ያሉት ኃላፊው በክልሉ በበጋ ወራትም የበጎ ፈቃድ ሥራዎችን ለማስቀጠል ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል፡፡

የብልጽግና ፓርቲ ዓላማ ሰው ተኮር እሳቤን እና በጎነትን ባሕል ማድረግ መሆኑን በመጥቀስ አሁን ላይ የበጎ ፈቃደኝነት አገልግሎት ባሕል እየሆነ መምጣቱም አስገንዝበዋል፡፡

የአማራ ክልል ሴቶች፣ ወጣቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ብርቱካን ሲሣይ በበኩላቸው÷ በአማራ ክልል በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ34 ቢሊየን ብር በላይ ሃብት ማዳን መቻሉን ገልፀዋል፡፡

እንደ ኃላፊዋ ገለፃ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ9 ሺህ 800 በላይ ደረጃቸውን የጠበቁ ቤቶች ተገንብተው ለአገልግሎት የበቁ ሲሆን ከ20 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ቤቶች ደግሞ እድሳት እና ጥገና ተደርጓል።

በክረምት ወራት ከ815 ሺህ በላይ ደርዘን ደብተር እና ሌሎች የትምህርት ቁሳቁስች ድጋፍ መደረጉንና በ100 ሺዎች ለሚቆጠሩ ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት መሰጠቱን ተናግረዋል።

በተጨማሪም 157 ሺህ ለሚጠጉ ወጣቶች የኢትዮ ኮደርስ ሥልጠና መሰጠቱን እና ከ38 ሺህ በላይ ዩኒት ደም በመሰብሰብ የእናቶችን ሕይወት መታደግ መቻሉን ጠቅሰዋል፡፡

በበጋው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የተተከሉ ችግኞችን በመንከባከብ፣ የግብርና ምርቶችን በአግባቡ በመሰብሰብ፣ የትምህርት ሥራን በማጠናከር፣ ሰላምን በመጠበቅ እና አቅመ ደካሞችን በመደገፍ የተጀመረውን ንቅናቄ በተሻለ ቁርጠኝነት እንዲቀጥልም ጥሪ አቅርበዋል።

#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ

በደሳለኝ ቢራራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.