Fana: At a Speed of Life!

የኢንዱስትሪው ህዳሴ፡ ከስልጣኔ ታሪክ ወደ ስልጣኔ ጉዞ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በታሪኩ አይቶት የማያውቀውን የመዋቅርና የማምረት አቅም ሽግግር እያደረገ ይገኛል።
በመደመር የኢኮኖሚ ፍልስፍና በተመሩና በተተገበሩ አጠቃላይ ሀገራዊ የማክሮ-ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ፣ አምራቹ ኢንዱስትሪ የሀገር ውስጥ አቅምን እና ፈጠራን መሰረት ከማድረግ ጋር ተጣጥሞ የእድገትና ብልጽግና ጉዞው በከፍተኛ ፍጥነት በመጓዝ ላይ ይገኛል፡፡
ይህ ዕጣ ፈንታን የሚቀይር የስኬት ጉዞና የአምራች ኢንደስትሪው አብዮት የሀገሪቷን ሁለንተናዊ ገጽታ እየቀየረው ይገኛል፡፡
ለበርካታ ዓመታት የሀገራችን የማምረት አቅም ተዳክሞ፣ ገበያው በውጪ ምርቶች ላይ ብቻ ጥገኛ ሆኖ የቆየ ቢሆንም፣ በ “ኢትዮጵያ ታምርት” ሀገራዊ ንቅናቄና በመደመር እይታ በተዘረጉ ፖሊሲዎች የተነሳ በአምራች ኢንደስትሪው ዘርፍ ትልቅ አብዮት ተቀስቅሷል።
ቀደም ሲል በውጪ ምንዛሪና በጥሬ ዕቃ እጥረት ምክንያት ሥራ አቁመው የነበሩ በርካታ ግዙፍና መካከለኛ አምራች ኢንደስትሪዎች ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ ተመልሰዋል።
ከዚህ ቀደም በቢሊየን ዶላሮች ወጪ ይወጡባቸው የነበሩ የጨርቃጨርቅ፣ የቆዳ፣ የምግብና መጠጥ፣ የኮንስትራክሽን ቁሳቁሶች እንዲሁም የመድኃኒት ምርቶች አሁን በሀገር ውስጥ ጥራት ባለው ሁኔታ መመረት ጀምረዋል።
በቴክኖሎጂና በክህሎት ሽግግር ረገድም፤ ዘመናዊ ማሽነሪዎችን በመጠቀምና የሀገር ውስጥ የሰው ኃይልን አቅም በመገንባት የምርት ጥራትና ብዛት በከፍተኛ ደረጃ አድጓል።
በመደመር እሳቤ የተቀረፀው የኢኮኖሚ ማሻሻያ ዋና ትኩረት “አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርትን” (GDP) ማሳደግና የማምረት አቅምን መጨመር ነበር።
ይህ እሳቤ አምራቹን ማህበረሰብ፣ ባለሀብቱንና መንግሥትን በማስተሳሰር አስደናቂ ውጤት አስመዝግቧል፤የኢንደስትሪ ፓርኮች የማምረት አቅማቸውን ወደ ላቀ ደረጃ አሸጋግረዋል።
በግብርናና በኢንደስትሪ ትስስር የግብርና ምርቶችን ለኢንደስትሪ ጥሬ ዕቃነት በስፋት ማቅረብ መቻሉ የአግሮ-ፕሮሰሲንግ ኢንደስትሪውን የምርት መጠን በእጥፍ እንዲያድግ አድርጎታል።
የኢንደስትሪው ዘርፍ ለሀገራዊ ምርት ያለው አስተዋጽኦ በከፍተኛ ሁኔታ ያደገ ሲሆን፣ ሀገሪቱ በአፍሪካ ፈጣንና ዘላቂ እድገት የሚያስመዘግብ ኢኮኖሚ ባለቤት እንድትሆን አስችሏታል።
የአምራች ኢንደስትሪው እድገት በቀጥታ በሀገሪቱ የውጪ ንግድ (ኤክስፖርት) እና በውጪ ምንዛሪ ግኝት ላይ ከፍተኛ ውጤትን አምጥቷል፡፡
ቀደም ሲል ከተወሰኑ ያልተቀነባበሩ የግብርና ምርቶች ይገኝ የነበረው የውጪ ምንዛሪ፣ አሁን ያለቀላቸው የኢንደስትሪ፣ የማዕድንና የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በማካተቱ በከፍተኛ ሁኔታ አድጓል።
በፈጠራና በጥራት የታገዙ የአምራች ኢንደስትሪ ምርቶች ወደ አውሮፓ፣ አሜሪካ፣ እስያና የእርስ በእርስ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና በስፋት መላካቸው ሀገሪቱ የምታገኘውን የሃርድ ከረንሲ ገቢ በከፍተኛ መጠን አሳድጎታል።
ማክሮ-ኢኮኖሚያዊ ማሻሻያውና የተረጋጋው የኢንቨስትመንት ምህዳር በርካታ ዓለም አቀፍ ግዙፍ ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው መዋዕለ ነዋያቸውን እንዲያፈሱ መንገድ ከፍቷል።
የኢትዮጵያ የአምራች ኢንደስትሪ እድገት አብዮት የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ምሰሶ ያጠናከረና ወደ ተሻለ የብልጽግና የጉዞ ምዕራፍ ያሸጋገረ ታሪካዊ እርምጃ ነው።
በመደመር እሳቤ መሪነት በቁርጠኝነት የተከናወኑት ተግባራት ኢትዮጵያ የነበራትን የውጪ ምርቶች ጥገኝነት ምዕራፍ ዘግተው፣ እራሷን የምትመግብ፣ የምታመርትና በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ ተወዳዳሪ የሆነች፤ የቀደምት ስልጣኔ ባለቤትና የመጪው ስልጣኔ ተምሳሌት የሆነች ዘመናዊ ሀገር እንድትሆን መሠረት ጥለዋል።
በመልካም ፈቃዱ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.