ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በጀግኖች ቀን ብሔራዊ በዓል ላይ ለመታደም ኬንያ ገቡ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጀግኖች ቀን ብሔራዊ በዓል ላይ ለመታደም ኬንያ ገብተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ለኬንያ ነፃነት፣ ሉዓላዊነትና ልማት የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ጀግኖች ክብር በሚሰጥበት የማሹጃ ቀን (የጀግኖች ቀን) ብሔራዊ በዓል አከባበር ላይ በክብር እንግድነት ለመታደም ኤልዶሬት ኬንያ መግባታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡