Fana: At a Speed of Life!

እኛ ትልቅ ሀገርና ትልቅ ህዝቦች ነን – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) እኛ ትልቅ ሀገርና ትልቅ ህዝቦች ነን፤ ይህንን ለዓለም ማሳየት አለብን አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ የኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽንን ጎብኝተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ ለልጆቻችን አስተማማኝ መሰረት በማስቀመጥ በኒውክሊየር፣ በስፔስ እና በኤአይ ነገ ዓለም በሚወዳደርባቸው መስኮች ኢትዮጵያን ማዘጋጀት አስፈላጊ ነው፡፡

ለዚህ ስራ ከሰላሳ በላይ ቦታዎች በባለሙያዎች ተጠንተው እና የውጭ ተቋማት የቦታውን አዋጭነት አረጋግጥው አሁን ላይ ዲፓርትመንቶችን ለይቶ ፕሮጀክት ለመስራት የሚያስችል ቁመና ላይ እንገኛለን ብለዋል፡፡

እኛ ትልቅ ሀገርና ትልቅ ህዝቦች ነን፤ ይህንን ለዓለም ማሳየት አለብን ያሉት ሲሆን፤ ሰላሳ ሚሊየን ተማሪ ያላት ሀገር ዛሬ ድሃ ብትሆን የዛሬ አስር አመት ልጆቿ ያላትን የተፈጥሮ ጸጋ አውጥተው ከፍተኛ ሀብት እንደሚፈጥሩ ገልጸዋል፡፡
ለልጆቻችን እኛ ጀምረንና አዘጋጅተን ከቆየናቸው እነሱ ጨምረው የኢትዮጵያን ብልጽግና ያረጋግጣሉ ነው ያሉት፡፡

በትዕግስት ግዛቸው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.