Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል ከ2 ነጥብ 8 ሚሊየን በላይ ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሠራ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል ከ2 ነጥብ 8 ሚሊየን በላይ ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሠራ ነው አለ የክልሉ ኢንዱስትሪና ኢንተርፕራይዝ ቢሮ፡፡
የቢሮው የሥራ ዕድል ፈጠራ ዳይሬክተር አቶ ተማም ሁሴን ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት፤ በክልሉ የሚገኙ ዜጎች ከሥራ ፍለጋ ወደ ሥራ ፈጠራ በመሸጋገር ለራሳቸውና ለሌሎች የሥራ ዕድል እየፈጠሩ ይገኛሉ፡፡
ባለፈው የበጀት ዓመት በክልሉ ከ2 ነጥብ 7 ሚሊየን በላይ ዜጎች የሥራ ዕድል ማግኘታቸውን ገልጸው፤ በዘንድሮው በጀት ዓመት ደግሞ ከ2 ነጥብ 8 ሚሊየን በላይ ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡
ሥራ ፈላጊ ወጣቶችን በተለያዩ የሥራ ፈጠራ ዘርፎች በማደራጀት፣ የብድርና የሥራ ቦታ ድጋፍ በማመቻቸት እንዲሁም የገበያ ትስስር በማመቻቸት እየተሠራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ከዚህ ስራ እድል ፈጠራ ጋር በተያየዘ በጅማ ከተማ የሚገኙ የስራ እድል ፈጠራ ተጠቃሚዎች እንዳሉት፤ ከሥራ ፍለጋ ተስፋ መቁረጥ ወደ ራስን መቻልና ለሌሎች የሥራ ዕድል መፍጠር ተሸጋግረናል፡፡
ከወጣቶቹ መካከል ፎዚያ ከድር ከዓመት በፊት ሥራ በማጣት ተስፋ ቆርጣ እንደነበር በማስታወስ፤ ዛሬ ላይ በእንጨት ቅርጻ ቅርጽ ሥራ በመሰማራት ራሷን ከመቻል ባለፈ ለሌሎችም የሥራ ዕድል መፍጠ አንደቻለች ገልጻለች።
አብዱረዛቅ ሸውሞሎ በበኩሉ ከሦስት ጓደኞቹ ጋር በመደራጀት በለውዝ ቅቤ ምርት ላይ መሰማራቱን በመጠቆም፤ የተደረጉ ድጋፎችም ውጤት ማምጣታቸውን ነው የገለጸው፡፡
በተስፋሁን ከበደ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.