Fana: At a Speed of Life!

የሠራዊቱ የሕዝብ ደጀንነት በትግራይ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የሀገር መከላከያ ሠራዊት ሀገርን ከውጭ ባዳዎች እንዲሁም ከውስጥ ባንዳዎች ሴራ የመከላከልና የኢትዮጵያን ሉዓላዊነቱን የማስጠበቅ ታሪካዊ ኃላፊነቱን በጀግንነት እየተወጣ ይገኛል።
ሠራዊቱ ከዚህ ባሻገር ከሕዝቡ ጎን በመሰለፍ የልማት፣ የሰላም እና የመረዳዳት ምዕራፍ በማስመዝገብ የሕዝብ ልጅነቱን እያረጋገጠ ይገኛል።
በተለይም ሠራዊቱ በትግራይ ክልል ሕዝቡን ከማረጋጋትና ሰላሙን ከማስጠበቅ ባለፈ በሁለንተናዊ ማህበራዊ ሕይወት ውስጥ ንቁ ተሳትፎ እያደረገ ነው።
የምዕራብ ዕዝ አብዲሳ አጋ ክፍለ ጦር፣ የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ሬጅመቶች እና የምዕራብ ዕዝ ፅናት ክፍለ ጦር አባላት ይህንን እውነታ በተግባር ለማሳየት አብነት ናቸው።
በትግራይ ክልል የሚገኙ አርሶ አደሮች በጤና እክል፣ በሰው ሃይል እጥረት እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች የደረሰውን ሰብል በወቅቱ ለመሰብሰብ ከፍተኛ ፈተና ገጥሟቸው ነበር።
ይህንን የሕዝብ ሰቆቃ የተረዳው የጀግናው መከላከያ ሠራዊት አባላት የጦር መሳሪያቸውን አስቀምጠው የእርሻ መሳሪያ በመያዝ ወደ ማሳ ወርደዋል።
የአርሶ አደሮቹን የደረሰ የጤፍ ሰብል በመሰብሰብ ለአርሶ አደሮቹ ትልቅ እፎይታን ሰጥተዋል። ሰብላቸው ደርቆ እየረገፈባቸው ከነበረበት ከባድ ጭንቀት የተላቀቁት አርሶ አደሮችም ሰራዊቱ ባደረገላቸው የሰብል ማህበራዊ ድጋፍ የተሰማቸውን ልባዊ ደስታና ምስጋና ገልጸዋል።
ሠራዊቱ ለበርካታ ዓመታት ሀገራቸውን በውትድርና አገልግለው በልዩ ልዩ ምክንያት ከሠራዊቱ የተሰናበቱ የቀድሞ የሠራዊት አባላትንም በማገዝ ከሕዝብ የተገኘ ቁርጠኛ የሕዝብ ልጅነቱን አረጋግጧል።
በግዳጅ ቀጣና አካባቢ የሚገኝን ማህበረሰብ በሁለንተናዊ መልኩ ማገዝና መተባበር የመከላከያ ሠራዊት የተልዕኳቸው አንዱና ዋናው አካል መሆኑን በተግባር አስመስክረዋል።
ሰራዊቱ ከሕዝብ የወጣ በመሆኑ ከሕዝብ ጋር ያለው ትስስር ሊለያይ የማይችል ነው። ሕገ-ወጡን የህወሃት ቡድን በመደምሰስ የተገኘውን አንጻራዊ ሰላም ወደ ላቀ ልማትና ማህበራዊ ትስስር ማሸጋገር አሁን ላይ ዋናው የትኩረት አቅጣጫ ሆኗል።
በትግራይ የተፈጠረው ሰላም አርሶ አደሩ ስጋት ሳይኖረው ሰብሉን እንዲያጭድና እንዲያከማች ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል።
የኢትዮጵያ የሃገር መከላከያ ሠራዊት የሀገርን ዳር ድንበር በማስጠበቅ ታሪክ ከመሥራት ባሻገር ከሕዝቡ ጋር ባለው ጥልቅ ፍቅር እና አጋርነት የሕዝብ እውነተኛ መታመኛና አለኝታነቱን ዳግም አስመስክሯል፤ እያስመሰከረም ይገኛል።
በሶስና አለማየሁ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.