Fana: At a Speed of Life!

በመቐለ ከተማ በኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ዙርያ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 4፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የመቐለ ከንቲባ ሽሻይ አማረ (ዶ/ር) እና የከተማዋ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፀጋዘኣብ ኪዳኑ በኮሪደር ልማት እንቅስቃሴዎች ዙሪያ ከሀይማኖት አባቶችና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር ተወያይተዋል።
በውይይቱ የመቐለ ከንቲባ ሽሻይ አማረ (ዶ/ር) እና የመቐለ ኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ፀጋዘኣብ ኪዳኑ ተገኝተው ማብራሪያና ገለፃ አድርገዋል።
በዚህም ፕሮጀክቱ እንደ መነሻ ፕሮጀክት መጀመሪያ ላይ ከመኖሪያ አካባቢው ብዙም ያልተቀራረበና የመኖሪያ ቤቶችን እና ተቋማትን በማይጎዳ መልኩ ለመስራት ቅድሚያ የተሰጠበት መሆኑ ተጠቅሷል።
በተጨማሪም ለወጣቶች የሥራ ዕድል ተጠቃሚነትን ማሳደግ ብሎም በየደረጃው ያለ አመራር ጠንካራ የሥራ ባህል እንዲያዳብር ማስቻል ቅድሚያ ትኩረት እንደተደረገበት ተገልጿል።
በአጠቃላይ ማህበረሰቡ የኮሪደር ልማቱ በፍጥነት እንዲጀመር ያለው ፍላጎት መነሻ በማድረግ የክፍለ ከተሞች አመራሮችም በቁርጠኝነት እንደሚያግዙ በሰፊው ሀሳብ አቅርበዋል።
ውይይቱ ከንግድ ማህበረሰብ፣ ከአካዳሚክ ባለሙያዎች እና ከተለያዩ የማህበረሰቡ ክፍል ተወካዮችም ይቀጥላል።
በግዛቸው ግርማዬ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.