የአፍሪካ የወጪ ንግድ ዕሴትን ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 14፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፍሪካ የወጪ ንግድ ዕሴትን ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡
‘በመላው አፍሪካ የተመረተ፤ አንድ ገበያ፣ ብዙ የሕግ ማዕቀፎች’ በሚል መሪ ሀሳብ የ2026 የአፍሪካ የንግድ ልማት ፎረም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።
ከፎረሙ ጎን ለጎን የአፍሪካ የወጪ ንግድ ዕሴትን ማሳደግ ላይ ያተኮረ ከፍተኛ ውይይት ተካሂዷል።
በውይይቱ የትሬድማርክ አፍሪካ የቦርድ ሰብሳቢ የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትርና አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና (AfCFTA) ዋና ጸሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ እንዲሁም የፊንላንድ የዓለም አቀፍ ንግድ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያርኖ ሲሪያላ ተሳትፈዋል።
በአፍሪካ አንድ ወጥ ገበያ ለመፍጠር የተለያዩ የንግድ ደንቦችን ማቀናጀትና የአህጉሪቱን የወጪ ንግድ ተወዳዳሪነት ማሳደግ ወሳኝ መሆኑ በመድረኩ ተመላክቷል።