Fana: At a Speed of Life!

አየር ኃይል በኢትዮጵያ ላይ የሚቃጡ ጥቃቶችን በማክሸፍ ታሪክ እየሰራ ይገኛል – ሌ/ጄኔራል ይልማ መርዳሳ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 15፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር ኃይል የዘመኑን የቴክኖሎጂ አቅሞችን በመታጠቅና የሰው ኃይሉን በማብቃት በሀገራችን ላይ የሚቃጡ ጥቃቶችን በማክሸፍ ታሪክ እየሰራ ይገኛል አሉ የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ይልማ መርዳሳ።

ሌተናል ጀኔራል ይልማ መርዳሳ የአየር ኃይል የ91ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን አሥመልክቶ በሰጡት በመግለጫ፤ በድል የዘለቀው አየር ኃይሉ የዘመኑን የቴክኖሎጂ አቅሞችን በመታጠቅና የሰው ኃይሉን በማብቃት በሀገራችን ላይ የሚቃጡ ጥቃቶችን በማክሸፍ ታሪክ እየሰራ ነው ብለዋል።

የ91ኛ ዓመቱ የምስረታ በዓልም “በድል እና በመስዋዕትነት የደመቀ የኢትዮጵያ ሰማይ አለኝታ” በሚል መሪ ሃሳብ ሕዳር 20 እና 21 ቀን 2019 ዓ.ም እንደሚከበር ጠቁመዋል።

ሕዳር 20 ቀን 2019 ዓ.ም በቢሾፍቱ ከተማ በርካታ ዓለም አቀፍ አትሌቶች የሚሳተፉበት የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ “አየር ኃይላችን መመኪያችን” በሚል መሪ ሃሳብ እንደሚካሄድም አንስተዋል።

የኢፌዴሪ አየር ኃይል በየዓመቱ በቢሾፍቱ ከተማ የሚያደርገውን ዓለም አቀፍ የጎዳና ላይ ሩጫ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የተጠቆመ ሲሆን የ91ኛው ዓመት የምስረታ በዓል የክብር ቲሸርትም በሌተናል ጀኔራል ይልማ መርዳሳ በይፋ መመረቁን የመከላከያ ሠራዊት ኦንላይን ሚዲያ ለፋና ዲጂታል የላከው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.