አምባሳደር ወይንሸት ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዚዳንት ተወካይ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ ፣መስከረም 25 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቋሚ ተጠሪ አምባሳደር ወይንሸት ታደሰ ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዚዳንት ተወካይ ሉታዲክ ያኒኪ ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም የሁለቱን ሃገራት ግንኙነት ማጠናከር በሚቻሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።
አምባሳደር ወይንሸት የኢትዮጵያ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ የደረሰበትን ደረጃ እና ኢትዮጵያ በናይል ወንዝ ፍትሃዊ እና ምክንያታዊ አጠቃቀም ላይ ያላትን አቋም በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል።
የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዚዳንት ተወካይ ሉታዲክ ያኒኪ በበኩላቸው ኮንጎ በናይል ወንዝ አጠቃቀም ላይ ከኢትዮጵያ ጋር በቅርበት እንደምትሰራ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ኤምባሲ ቢኖራት ግንኙነቱን ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚያግዝ መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።