Fana: At a Speed of Life!

በሳዑዲ አረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ደህንነት መጠበቅ ዙሪያ ውይይት ተደረገ

አዲስ አበባ ፣መስከረም 26 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሳዑዲ አረቢያ የኢትዮጵያ አምባሳደር አብዱልአዚዝ ከሳዑዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ሳሚ ሳልህ ጋር በኢትዮጵያውያን ዜጎች ደህንነት መጠበቅ ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

አምባሳደር አብዱላዚዝ ውይይቱን ያደረጉት ሰሞኑን በሳኡዲ አረቢያ የሚኖሩ ዜጎች በአንዳንድ አካባቢዎች በአፈሳ ለእስር መዳረጋቸውን ተከትሎ ነው ተብሏል።

በውይይቱም ለችግሩ በአፋጣኝ እልባት እንዲሰጠው እና ዜጎች መብታቸውና ደህንነታቸው እንዲጠበቅ ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን በሳዑዲ አረቢያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያወጣው መረጃ ያመላክታል።

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.