ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በባህር ዳር ከተማ ለአካል ጉዳተኞች የዊልቼር ድጋፍ አደረጉ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በባህር ዳር ከተማ ለሚገኙ አካል ጉዳተኞች የዊልቼር ድጋፍ አድርገዋል።
የተደረገው የዊልቼር ድጋፍ አካል ጉዳተኞች ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ እንዲችሉ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ተብሏል።
በተመሳሳይ ቀዳማዊት እመቤቷ በባህርዳር ከተማ የሚገኘውን እየሩሳሌም የህጻናት እና ማህበረሰብ ልማት ድርጅት ጎብኝተዋል።
በተያያዘም የቀዳማዊ እመቤት ጽህፈት ቤት ከእየሩሳሌም የህጻናት እና ማህበረሰብ ልማት ድርጅት ጋር በመተባበር ፈቃደኛ ሴተኛ አዳሪዎችን ወደ መደበኛ
ህይወት ለመመለስ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል ተብሏል።
በዚህም አሁን ላይ በማዕከሉ 17 ሰልጣኞች የህይወት ክህሎት፣ የስነ ልቦና ማማከር አገልግሎት እና የሙያ ስልጠና እየተሰጣቸው ይገኛል፡፡
እስካሁን አራት ሴቶች ከቀደመ አኗኗራቸው ተላቀው ወደ ንግድ ስራ የተሰማሩ ሲሆን በቅርቡ 20 ሰልጣኞች ወደ ማዕከል ይገባሉ።
ባለፈው አመት የተጀመረው ይህ ፕሮጀክት ለአራት አመታት የሚቆይ ሲሆን 695 ሴቶችን ለማሰልጠን ታቅዷል።
በአላዛር ታደለ