ጠ/ሚ ዐቢይ የዓለም ምግብ ፕሮግራም የ2020 የኖቤል የሰላም ሽልማት በማሸነፉ የደስታ መልዕክት አስተላለፉ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የዓለም የምግብ ፕሮግራም የ2020 የኖቤል የሰላም ሽልማት በማሸነፉ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት የደስታ መልዕክት ለፕሮግራሙ ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ቤስሌይ የ2020 የሰላም ሽልማት በማሸነፋችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
የዓለም የምግብ ፕሮግራም ረሃብን ለመዋጋት ባደረገው ጥረት የፈረንጆቹ 2020 የሰላመ ኖቤል አሸናፊ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባለፈው አመት የሰላም የኖቤል ሽልማት አሸናፊ መሆናቸው የሚታወስ ነው፡፡