በሀረሪ ክልል በ78 ሚሊየን ብር ወጪ አስፋልት ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ
አዲስ አበባ ፣ መስከረም 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀረሪ ክልል በ78 ሚሊየን ብር ወጪ አስፋልት ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ።
የመንገድ ፕሮጀክቱ ከሀረር ኤረር በር እስከ ኤረር ወልድያ ያለው መንገድ ነው።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሩ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሚስራ አብደላን ጨምሮ ሌሎች የካቢኔ አባላትና ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍል ተወካዮች በተገኙበት ነው የመሰረት ድንጋይ የተቀመጠው።
ፕሮጀክቱ በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ የክልሉ መንገድ ባለስልጣን መግለጹን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡