ባለስልጣኑ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት 68 ኪሎ ሜትር ልዩ ልዩ መሠረተ ልማት ጥገና ስራዎችን አከናወነ
አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 12 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት 68 ኪሎ ሜትር ልዩ ልዩ መሠረተ ልማት ጥገና ስራዎችን ማከናወኑን አስታወቀ፡፡
ባለስልጣኑ በሶስት ወራት ውስጥ የአስፋልት መንገድ ጥገና 5 ኪሎሜትር፣ የፍሳሽ መስመሮች ጽዳትና ጥገና 54 ኪሎ ሜትር፣ ጠጠር መንገድ ጥገና 7 ኪሎ ሜትር፣ የእግረኛ መንገድና ከርቭ ስቶን ጥገና 2 ኪሎ ሜትር፣ የመንገድ መብራት ጥገና በቁጥር 3 ሺህ 412 ስራዎች ማከናወኑን ገልጿል፡፡
በተጨማሪም ድልድይና ድጋፍ ግንብ እና የእግረኛ መከላከያ አጥር የጥገና ስራዎች ማከናወኑንም ከአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ መላክታል፡፡
በቀጣይም ባለስልጣኑ በአገልግሎት ብዛትና በልዩ ልዩ ምክንያት ለጉዳት የተዳረጉ የመንገድ መሠረተ ልማቶችን የጥገና ስራ በማከናወን በመዲናዋ የተሻለ የመንገድ መሰረተ ልማት እንዲኖር እና የትራፊክ ፍሰቱ የተሳለጠ እንዲሆን የጥገና ስራውን በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥልም ነው የገለጸው፡፡
