Fana: At a Speed of Life!

በባንግላዴሽ በከፍተኛ ቀዝቃዜ የ50 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በባንግላዴሽ በተከሰተ ከፍተኛ ቀዝቃዜ የ50 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተነገረ።

እሁድ በሀገሪቱ ሰሜን ጠረፍ በምትገኘው ቱቶልያ ከተማ ውስጥ 4 ነጥብ 5 ዲግሪ ሴልሺየስ የተመዘገበ ዝቅተኛው የሙቀት መጠን   መሆኑን ተገልጿል።

በመላው ሀገሪቱ ቀዝቃዛ የአየር ጠባይ መስፋፋቱን ተከትሎ ቢያንስ የ50 ሰዎች  ህይወት ማለፉን የሀገሪቱ ባለስልጣናት ገልጸዋል፡፡

17 ሰዎች በከባድ የመተንፈሻ በሽታ እና 33ቱ ደግሞ በተቅማጥ በሽታ ህዳር 1 እስከ ታህሳስ 28 ድረስ ህትወታቸው ማለፉን  አይሻ አክሃተር የሀገሪቱ የጤና ዳይሬክቶሬት ከፍተኛ ባለስልጣን ተናግረዋል።

ሆስፒታሎች እንደ ኢንፍሉዌንዛ፣ ሳንባ ምች እና ከጉንፋን ጋር ተያይዘው በሚሰቃዩ ሰዎች የተጨናነቁ መሆናቸውንም አስረድተዋል።

ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው፣ በተለይም ጉልበት ሠራተኞች፣ ሕፃናትና አዛውንቶች እንደሳምባ ምች ላሉት በሽታዎች  የተጋለጡ ናቸው ተብለዋል።

ከቀዝቃዛው አየር ጋር ነፋሻማ እና ጥቅጥቅ ጭጋግ ጋር ተያይዞ ለተወሰኑ ቀናት ይህ የአየር ሁኔታ ሊቀጥል እንደሚችል የሀገሪቱ የአየር ትንበያ ጽህፈት ቤቱ መግለጹም ተነግሯል።

ይህ ከባድ ጭጋግማ የአየር ሁኔታ በርካታ በረራዎች እንዲቀየሩና እና ሌሎቹም እንዲዘገዩ አንዳስገደዳቸው የአየር መንገዱ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

በከፍተኛ ቅዝቃዜው ሰዎች ከቤት መውጣት በመቸገራቸው የተሳፋሪዎች ቁጥር በእጅጉ መቀነሱም ነው የተነገረው።

ምንጭ፦ አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.