በህግ የማስከበር ግዳጅ ላይ ለሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት የድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ህዳር 9፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በትግራይ ክልል በህግ የማስከበር ግዳጅ ላይ ለሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው።
የድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብሩን ያዘጋጁት የአዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን እና የከተማዋ መሬት ማኔጅመንት ቢሮ ናቸው።
በገቢ ማሰባሰቢያው ላይ የተገኙት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ዣንጥራር አባይ ሰራዊቱ ህግን ለማስከበር ለሚወጣው ግዳጅ በከተማ አስተዳደሩ ድጋፎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን ገልፀዋል።
በዚህ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ላይ በከተማዋ የሚገኙ ባለሀብቶች ተሳታፊዎች ናቸው።
በለይኩን አለም