Fana: At a Speed of Life!

የከተሞችን ምጣኔ ሃብት ለማሳደግና ስራ አጥነትን ለመቀነስ ለኢንዱስትሪ ዘርፍ መሰረት መጣል ያስፈልጋል – ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 13 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የከተሞችን ምጣኔ ሃብት ለማሳደግና ስራ አጥነትን ለመቀነስ ለኢንዱስትሪው ዘርፍ ትኩረት መስጠት እንደሚያስፈልግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ።
የአነስተኛና መካከለኛ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ልማት የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ የተገኙት ምክትል ከንቲባዋ ለኢንዱስትሪ ልማት መሰረት ለመጣል የጥቃቅንና አነስተኛ ማምረቻ ዘርፉን ማሳደግና ማስፋት እንደሚገባ አንስተዋል።
በዘርፉ በርካታ የስራ ዕድል በመፍጠር ስራ አጥነትን መቀነስ ዋነኛው የትኩረት መስክ መሆን እንዳለበትም አጽንኦት ሰጥተዋል።
የአነስተኛና መካከለኛ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ዘርፉን በማሳደግ ስራ አጥነትን ለመቀነስ በሚደረገው ጥረት የሚስተዋሉ ችግሮችን መለየትና በቅንጅት መፍታት እንደሚገባም አሳስበዋል።
በውይይት መድረኩ የፌደራልና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ ተቋማት የስራ ኃላፊዎች ታድመዋል።
በ2013 በጀት ዓመት ለሚከናወኑ ተግባራት የሚያስፈልጉ ድጋፎችን መስጠት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት እንደሚካሄድም ይጠበቃል።
በአነስተኛና መካከለኛ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ዘርፉ የነበሩ ችግሮች ተለይተው የሚፈቱበት አቅጣጫ እንደሚቀመጥም ኢዜአ ዘግቧል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.