Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል ሸበሌ ዞን ቤርአኖ ወረዳ በቆላ የመስኖ ስንዴ እየለማ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 14፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል ሸበሌ ዞን ቤርአኖ ወረዳ በቆላ የመስኖ ስንዴ እየለማ መሆኑን የክልሉ ከፍተኛ የሰብል ተመራማሪ ዶክተር አብዲ አህመድ ተናግረዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ በወረዳው 500 ሄክታር መሬት ተሸፍኖ ቡቃያው በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ልማቱ ከቀበሌ እስከ ፌዴራል ሁሉንም አካላት ባሳተፈ መልኩ በቅንጅት እየተከናወነ መሆኑን የገለፁት ተመራማሪው ዓላማው በመስኖ የቆላ ስንዴ ምርታማነትን ደረጃ ለመለካትና አርብቶ አደሩን ለማስተማርና ለማላመድ ነው ብለዋል።

በአካባቢው ያሉ አርብቶ አደሮችም ቀደም ሲል ውሃና መሬት እያለ ያለጥቅም የቆየው መሬታቸው ካለፈው ዓመት ጀምሮ በስንዴ በመልማቱ ከፍተኛ ጥቅም እንዳገኙ መናገራቸውን ከሶማሌ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.