Fana: At a Speed of Life!

ባሌን የኦሮሚያ ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ መንግሥት እየሰራ እንዳለ አቶ አዲሱ አረጋ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 14፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ክላስተር አስተባባሪ በአቶ አዲሱ አረጋ የተመራው የኦሮሚያ ክልል መንግስት አመራር በባሌ ዞን ሮቤ ከተማ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ጎብኝቷል፡፡

በሮቤ ከተማ 60 ፕሮጀክቶች ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ ተመድቦላቸው እየተሰሩ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

በጉብኝቱ አቶ አዲሱ ኦሮሚያ ሠላምና ልማት ላይ እንዳለች ተናገረዋል፡፡

ከአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ሞት በኋላ በኦሮሚያ ሁከት ከተከሰተባቸው ቦታዎች ውስጥ ባሌ ሮቤ አንዱ መሆኑ ይታወሳል፡፡

የልዑካን ቡድኑ በሮቤ እየተገነባ ያለውን የልዩ ክህሎት ትምህርት ቤት ጎብኝቷል።

ይህ ፕሮጀክት የኦሮሚያ መንግሥት በቅርብ ጊዜ ሊያስፈጽም ካቀዳቸው 100 የ ‹‹ኢፋ ቦሩ›› ትምህርት ቤቶች ግንባታዎች ውስጥ አንዱ ነው፡፡

የዚህ ፕሮጀክት ሥራ በሮቤ የተጀመረው ከአንድ ወር ተኩል በፊት ሰሆን አሁን ላይ የስራው 40% መገባደዱ ተነግሯል።

ይህ የልዩ ክህሎት ትምህርት ቤት በቀጣይ አራት ወራት ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ ለመጪው ዓመት የትምህርት ዘመን ዝግጁ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡

ትምህርት ቤቱ በአሁኑ ጊዜ በሮቤ እየተሰሩ ካሉ ሦስት ትምህርት ቤቶች አንዱ ሲሆን፣ መንግሥት ከተማዋ ያለባትን የትምህርት ቤት እጥረት በእጅጉ ይቀንሳል ብሎ እንደሚያምን አቶ አዲሱ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም በሮቤ እየተሰራ ያለውን አዲስ የባስ ተርሚናልና የኢንዱስትሪ ፓርክ፣ የሴቶችና ህጻናት ህክምና አዲስ ሆስፒታል፣ የ15 ኪሎሜትር የሮቤ ከተማ የአስፓልት መንገድ ሥራ ተጎብኝቷል፡፡

ባሌ ያላትን የቱሪዝም ሐብት ለማሳደግ እና ባሌን የኦሮሚያ ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ መንግሥት እየሰራ እንዳለ የገለጹት አቶ አዲሱ፣ በቅርቡ ደረጃቸውን የጠበቁ ሁለት ሆቴሎች በባለሐብቶች በዞኑ እንደሚገነቡም ተናግረዋል፡፡

መንግሥት ለቱሪዝም ትኩረት ከመስጠቱ የተነሳ በቅርቡ የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን በማቋቋም በሰፊው እየተንቀሳቀሰ እንዳለ ገልጸዋል፡፡

በልማት ሥራዎቹ ላይ በነቂስ የተሳተፈውን ህዝብ፣ ሥራዎቹን በንቃት የተከታተሉትን ኃላፊዎችና በመልካም የተጉ የሥራ ተቋራጮችን አመስግነዋል፡፡

ከዚህ በኋላ ሥራን ወደኋላ የሚጎትቱ ተቋራጮች ላይ እርምጃ ይወሰዳል፤ እንደከዚህ በፊቱ የመሠረት ድንጋይ አስቀምጠን እዚያው አንተውም ማለታቸውን ከኦሮሚያ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጀ ያሳያል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.